በአመራር ስነ-ምግባር ዙርያ ለተቋሙ መካከለኛ አመራሮች ስልጠና ተሠጠ፡፡

በአመራር ስነ-ምግባር ዙርያ ለተቋሙ መካከለኛ አመራሮች ስልጠና ተሠጠ፡፡ =================== አዲስ አበባ 20/04/2016ዓ.ም(ንቀትሚ) በአመራር ስነ-ምግባር ዙርያ ለሚኒስትር መስሪያ ቤቱ መካከለኛ አመራሮች በአዳማ ከተማ ስልጠና ተሰቷል፡፡ በስልጠናው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት በንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር የሚኒስቴር ፅህፈት ቤት ሃላፊ ወ/ሮ ፍሬህይወት ወልደማርያም የንግድ ሴክተሩ ትልቅ ሃላፊነት የተጣለበትና የሚሠጡ አገልግሎቶች ከማህበረሠቡ ጋር የሚገናኙ በመሆናቸው ሙያዊ ስነ-ምግባርን በተላበሰ እና በህዝብ አገልጋይነት ስሜት ስራን ማከናወን እንደሚገባ ገልፀዋል፡፡ ስልጠናው የአሰራር ስርዓትን በማሻሻል፣ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመፍታትና ውጤታማነትን ለማሳደግ እንደሚያግዝም ተናግረዋል፡፡ ሙያዊ ስነ-ምግባር ያለው አመራር ሙያዊ ስነ ምግባር ያለው ባለሙያን መፍጠር እንደሚችል ገልፀው፡፡ የተቋሙ መካከለኛ አመራሮች ሙያዊ ስነ ምግባርን በመተግበር እና ወደ ሠራተኛው በማውረድ የተቋሙን ውጤታማነት የማሳደግ ሃላፊነት አለባቸው ሲሉ ሀላፊዋ ተናግረዋል። የአመራር ስነ-ምግባር በሚል ርዕስ የተሠጠው ስልጠና የቡድን ውይይቶችን ፣ አለም አቀፍ ተምክሮዎችን እና ልምድ ልውውጦችን በማካተት የቀረበ ነው።

Share this Post