ኤሌክትሮኒክስ የነዳጅ ግብይት ስርዓት የነዳጅ ብክነትንና ህገ-ወጥ ግብይትን አስቀርቷል፡፡

ኤሌክትሮኒክስ የነዳጅ ግብይት ስርዓት የነዳጅ ብክነትንና ህገ-ወጥ ግብይትን አስቀርቷል፡፡

===============================

አዲስ አበባ 30/04/2016ዓ.ም (ንቀትሚ) ኤሌክትሮኒክስ የነዳጅ ግብይት ስርዓት በመተግበሩ በከተማው የነበረውን ህገ-ወጥ ግብይትና የነዳጅ ብክነት ማስቀረቱን የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ንግድ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ ገለጸ፡፡

ነዳጅ ከጅቡቲ ከተጫነበት ጀምሮ በአስተዳደሩ ስር በሚገኙ የነዳጅ ማደያዎች ደርሶ እስከሚራገፍበት ጊዜ ድረስ ዲጂታል የክትትል ሥርዓት በመዘርጋቱ እና ግብይቱም ሙሉ በሙሉ ዲጂታል በመደረጉ ህገ-ወጥ የነዳጅ ዝውውርና ግብይትን ማሰቀረት ተችሏል ሲሉ የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ንግድ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አሚኑ ጠሃ ተናግረዋል፡፡

በድሬዳዋ ከተማ ተዘዋውረን ያነጋገርናቸው የነዳጅ ማደያ ባለቤች በበኩላቸው ዲጂታል ስርዓቱ ስራቸውን እንዳቀለለላቸውና ገልጸው የቴሌ ብር የገንዘብ ዝውውር መዘግየት እና ከጂቡቲ እስከ ማደያዎች ያለው የነዳጅ እንቅስቃሴ የሚመራበት ስርዓት/system/ ላይ አልፎ አልፎ የሚስተዋለው የቴክኒክ ችግር ቢስተካከል እንዲሁም ግብይት በሚፈጸምባቸው የባንኮች እና የቴሌ ብር ሥርዓቶች የተፈጸመበት የነዳጅ ሽያጭ ሪፖርት/statement/ በሲስተሙ ቢታከልበት

እንደ ሀገር የሚያስገኘው ፋይዳ የላቀ ይሆናል የሚል አስተያየት ሰጥተዋል፡፡

የአስተዳደሩ ንግድ ጽ/ቤት በሁሉም ማደያዎች በየእለቱ ያለውን የነዳጅ መጠንና አይነት በሚዲያ ይፋ እያደረገ በመሆኑ ነዳጅ እያለ “የለም” በማለት በተጠቃሚዎች ላይ ይደርስ የነበረውን እንግልትና ጫና ማስቀረት መቻሉንም ከጽ/ቤቱ ያኝነው መረጃ ያመለክታል፡፡

Share this Post