ኢትዮጵያ የዓለም ንግድ ድርጅት አባል ለመሆን የምታደርገው ዝግጅት ተስፋ ሰጭ ውጤት እየታየበት ነው :- አቶ ካሳሁን ጎፌ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ዴኤታ

ኢትዮጵያ የዓለም ንግድ ድርጅት አባል ለመሆን የምታደርገው ዝግጅት ተስፋ ሰጭ ውጤት እየታየበት ነው :- አቶ ካሳሁን ጎፌ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ዴኤታ ===================== አዲስ አበባ 14/07/2016ዓ.ም (ንቀትሚ) ኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ የንግድ ግንኙነቷን ለማስፋፋት እና ተገማች የሆነ ገበያ ለማፈላለግ የሚያስችላትን የዓለም ንግድ ድርጅት አባልነት ጥያቄ ተቀብላ እያካሄደች ያለቸው የድርድር ሂደት ውጤት እየታየበት ነው ሲሉ በንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር የንግድ ትስስርና ወጪ ንግድ ፕሮሞሽን ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ካሳሁን ጎፌ ተናግረዋል፡፡ ሚኒስትር ዴኤታው እንደገለጹት ኢትዮጵያ የዓለም ንግድ ድርጅት አባልነት ድርድርን ከጀመረች ዓመታትን ብታስቆጥርም በተለያዩ ምክንያቶ የድርድር ሂደቱ አዝጋሚ ሆኖ ቆይቷል፡፡ አሁን ያለው የኢፌዲሪ መንግስት በሰጠው ትኩረት በተለይም ከባለፈው ዓመት ወዲህ እየተካሄዱ ያሉ የድርድር ሂደቶች ውጤት እየታየባቸው ነው፡፡ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ለህዝብ ተወካዮች ም/ቤት ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢዎች እና የንግድና ቱሪዝም ቋሚ ኮሚቴ አባላት በዓለም ንግድ ድርጅት የአባልነት ደርድር ሂደት እና በአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ ንግድ ቀጣና ስምምነት ዙሪያ በቢሾፍቱ ከተማ ስልጠና እየሰጠ ይገኛል፡፡ ስልጠናው የንግድ ድርድር ሂደቶቹን የበለጠ ክትትልና ድጋፍ በማድረግ በአሰራር ሂደት የሚያጋጥሙ መሰናክሎችን በመፍታ ረገድ አጋዥነታቸውን ለማጠናከር የሚያስችል ነው፡፡

Share this Post