የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ምርትና አገልግሎቶች ጥራት ለማስጠበቅ የሚያስችል የተቀናጀ የቴክኒክ ደንብ ትግበራ ማዕቀፍ ተፉራረመ

የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ምርትና አገልግሎቶች በወጣላቸው ደረጃ መሰረት እየተመረቱና አገልግሎት እየሰጡ መሆናቸውን ለማረጋጋጥ የሚያስችል የተቀናጀ የቴክኒክ ደንብ ትግበራ የመግባብያ ሰነድ ከተቆጣጣሪ ተቋማት ጋር ተፈራረመ፡፡

የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ሚኒስትር አቶ ገብረመስቀል ጫላ መንግስት የንግድና የግበይት ስርዓቱን ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ፣ ተወዳዳሪና ትርፋማ  ለማድረግ በርካታ አዳዲስ ዘመናዊ አሰራሮች እየተገበረ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

የኢትዮጵያን የምርትና አገልግሎት ደረጃ ለማሳደግ የጥራት መሰረተ ልማት ማዕከላት ከመገንባት ባሻገር በሰው ኃይልና በግብዓት መጠነ ሰፊ የአቅም ግንባታ ስራ እየተከናወነ መሆኑን ያነሱት ሚኒስትሩ የቁጥጥር ስርዓቱን ለማዘመንና የተቆጣጣሪ አካላትን አቅም ለማጎልበት  የቅንጅት ስራ እየተሰራ ይገኛል ብለዋል፡፡

የቴክኒክ ደንብ ቁጥጥር  በአንድ ሀገር ያለ ምርትና አገልግሎቶች በወጣላቸው ደረጃ መሰረት መመረታቸውንና አገልግሎቶች መስጠታቸውን የምናረጋግጥበት፣ የሀገር ጥቅም የምናስጠብቅበት በመሆኑ የትብብር ስምምነቱ አስፈላጊ መሆኑን ሚኒስትሩ ጠቁመዋል፡፡

የትብብር ስምምነቱ የተግባርና የኃላፊነት መደራረብን፣ የህግ ድግግሞሽን፣ የሀብት ብክነትን፣ የኃላፊነትና የተጠያቂነት አሰራርን ከማስፈኑ በተጨማሪ ቁጥጥር  ለሚደረግበት  ተቋም  ግልፅነት በመፍጠር በኩልም የትብብር ስምምነቱ አስተዋፅኦው ከፍተኛ እንደሚሆን ተገልጿል፡፡

Share this Post