የወጣቶች ፎረም የምክክር ጉባኤ ተካሄደ።

የወጣቶች ፎረም የምክክር ጉባኤ ተካሄደ። ======================= አዲስ አበባ 13/04/2016 ዓ.ም (የንቀትሚ) የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር የወጣቶች ፎረም የፎረሙ አባለት በተገኙበት በተለያዩ ጉዳዮች ላይ በአዳማ ከተማ ምክክር አድርገዋል:: በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ስራ አስፈጻሚ ወ/ሪት ግሩም እንዳለው የወጣቶች ፎረም በ2015 በጀት ዓመት የተመሰረተ መሆኑን ገልጸው ፎረሙ ወጣቶች በማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች የሚገጥሞቸውን ተግዳሮቶች በተቀናጀና በተደራጀ አግባብ ተገናኝተው የሚፈቱበት መሆኑን ተናግረዋል። በተቋሙ በሚዘጋጁ ዕቅዶች ፕሮግራሞችና ስትራቴጂዎች ውስጥ የወጣቶች ጉዳይ በማካተት መስራት እና ወጣቶችን ተጠቃሚ ማድረግ እንደሚገባም ተጠቁሟል፡፡ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ስራ አስፈጻሚ ከአልትራ ላይፍ ትሬዲንግ ሼር ካምፓኒ ጋር በመተባበር በተካሄደው መድረክ የፎረሙ መተዳደሪያ ደንብ፣የበጀት ዓመቱ 2ኛ ግማሽ ዓመት ዕቅድ፣ ለውጥና የወጣቶች ጉዳይ ማካተት ዙሪያ ሰነድ ቀርቦ ውይይት በመወያየት ተጠናቋል፡፡

Share this Post