ከሠኞ እስከ እሁድ ባለው የስራ ሰዓት የፈቃድ እድሳት አገልግሎቶችን ማግኘት እንደሚቻል ተገለፀ፡፡

ከሠኞ እስከ እሁድ ባለው የስራ ሰዓት የፈቃድ እድሳት አገልግሎቶችን ማግኘት እንደሚቻል ተገለፀ፡፡ ================ አዲስ አበባ 15/04/2016ዓ.ም (ንቀትሚ) በክልሎች ላይ ሲሠጡ የነበሩ የአስመጪነት እና የላኪነት የንግድ ምዝገባና ፈቃድ አገልግሎቶች እንደ ቀድሞው ወደ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ መመለሳቸውን ተከትሎ በሚኒስቴር መ/ቤቱ የሚሠጡ የንግድ ስራ መደቦች ላይ በበጀት አመቱ ከሀምሌ1/2015 ዓ.ም እስከ ታህሳስ 30/ 2016 ዓ.ም ድረስ የንግድ ስራ ፈቃድ ለሚያድሱ ተገልጋዮች ከሠኞ እስከ እሁድ በመንግስት የስራ ሰዓት የፈቃድ እድሳት አገልግሎቶችን በኦንላይን ማግኘት እንደሚችሉ የንግድ ስርዓትና ላይሠንሲንግ ዘርፍ መሪ ስራ አስፈፃሚ አቶ ጅራታ ነመራ ገልፀዋል፡፡ እንደ መሪ ስራ አስፈፃሚው ገለፃ በበጀት አመቱ 105 ሺህ የንግድ ስራ ፈቃድ እድሳት አገልግሎቶችን ለመስጠት መታቀዱን ገልፀው እቅዱን ለማሳካትና ቀልጣፍ አገልግሎትን ለተገልጋዮች ለመስጠት በቂ ዝግጅት መደረጉን ጠቁመዋል፡፡ ወቅቱ የእድሳት አገልግሎት የሚሰጥበት ከመሆኑ ጋር ተያይዞ በመጨረሻ ቀናት የሚከሰቱ የሲስተም ወረፋዎችን ለመከላከል እንዲቻል ተገልጋዮች የሚያስፈልጉትን መስፈርቶች በሟሟላት የንግድ ስራ ፈቃዳቸውን በቀሩት ቀናት አስቀድመው በኦን ላይን እንዲያድሱ መሪ ስራ አስፈፃሚው መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

Share this Post