የንግድ ቱሪዝምና ቋሚ ኮሚቴ በንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር እና በተጠሪ ተቋማቱ በመገኝት የመስክ ምልከታ አደረገ።

የንግድ ቱሪዝምና ቋሚ ኮሚቴ በንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር እና በተጠሪ ተቋማቱ በመገኝት የመስክ ምልከታ አደረገ። ======================= አዲስ አበባ 19/04/2016ዓ.ም (ንቀትሚ) የኤፌድሪ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የንግድ ቱሪዝምና ቋሚ ኮሚቴ በንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር እና ተጠሪ ተቋማቱ ባደረገው ምልከታ አሰራሮችን ቀልጣፋና ውጤታማ ለማድረግ እየተሰሩ ያሉ የሪፎርም ስራዎች ተጠናክረው ሊቀጥሉ ይገባል ብሏል። ቋሚ ኮሚቴው አሰራርን በማዘመን በቴክኖሎጂ የተደገፈ የአሰራር ስርዓት መዘርጋቱ፣ በጥራት መሰረተ ልማት ላይ እየተሰሩ ያሉ ስራዎች ፣ በወጪ ንግድ ላይ እየተገበሩ ያሉ የሪፎርም ስራዎች በጠንካራ ጎን የሚጠቀሱ መሆናቸውን አብራርቷል። ቋሚ ኮሚቴው በምልከታው አሰራሮችን የቃኝ ሲሆን ኮንትሮባንድ፣ የቁም እንስሳት ግብይት፣የገብያ ግልጸኝነትና እና የሸማች መብት ማስከበር ላይ የሚታዩ ክፍተቶች በቀጣይ ሊሻሻል ይገባል ሲል አቅጣጫ አስቀምጦባቸዋል። በሚኒስትር መስራ ቤቱ የሚሰሩ የልማት ስራዎችን፣ የህንጻ እድሳትን የጎበኝው ቋሚ ኮሚቴው የሚኒስቴር መስራ ቤቱን ሰራተኞችንም አወያይቷል::

Share this Post