የህንዱ ኩባንያ በኢትዮጵያ ኢንቨስት ለማድረግ በሚችልባቸው ጉዳዮች ላይ ከንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ጋር ውይይት አካሄደ

የህንዱ ኩባንያ በኢትዮጵያ ኢንቨስት ለማድረግ በሚችልባቸው ጉዳዮች ላይ ከንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ጋር ውይይት አካሄደ ====================== አዲስ አበባ 12/06/2016 (ንቀትሚ) Groboco Foodworks private Limited የተሰኘው የህንድ ኩባንያ በኢትዮጵያ ንግድና ኢንቨስትመንት ለመሰማራት ያለውን ፍላጎት በማሳየት በንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ተገኝቶ ውይይት አካሂዷል፡፡ በውይይቱም ኢትዮጵያ በንግድና ኢንቨስትመንት ያሏትን አማራጭ እድሎች፣ የንግድ ምዝገባና ፈቃድ አገልግሎት አሰጣጥ ሂደት፣ ህጋዊ የንግድ ማእቀፎች እንዲሁም የጥራት መሰረተ ልማትን አስመልክቶ በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ አመራሮች አማካኘነት ለድርጅቱ ተወካዮች ሰፊ ማብራሪያ ተሰጥቷል፡፡ Groboco Foodworks private Limited የተሰኘው የህንድ ኩባንያ በምግብ ማቀነባበር ላይ የተሰማራ ድርጅት ሲሆን በሀገራችንም በአፈር ማዳበሪያ፣ በአግሮ ፕሮሰሲንግ እና በኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ኢንዱስትሪ ለመሰማራት ፍላጎት አሳይቷል፡፡

Share this Post