የሀገራዊ የሸማቾች መብት ጥበቃ ማህበር የቦርድ አባላት ምርጫ እና ለሸማች ማህበራት አመራሮች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተካሄደ።

የሀገራዊ የሸማቾች መብት ጥበቃ ማህበር የቦርድ አባላት ምርጫ እና ለሸማች ማህበራት አመራሮች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተካሄደ። ==================== አዲስ አበባ 19/06/2016ዓ.ም (ንቀትሚ) ከሁሉም ክልሎችና የከተማ አስተዳደር ለተውጣጡ የሸማች ማህበራት አመራሮች በሸማቾች መብት ጥበቃ እና የሸማች ማህበራት ምንነትና አስፈላጊነት ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሠጠ፡፡ በመድረኩ የመክፈቻ ንግግድ ያደረጉት ሚኒስቴር ዴኤታ አማካሪ አቶ ግዛው ተክሌ በሀገር አቀፍ ደረጃ የሸማቾች መብት የሚያስከብሩ ማህበራትን ለማቋቋም ካለፈው አመት ጀምሮ ብዙ ስራዎች የተሠሩ መሆኑን ገልፀዋል፡፡ በግንዛቤ ማስጨበጫ መድረኩ ከሁሉም ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች ከተውጣጡ የሸማች ማህበራት አመራሮች ውስጥ ለሀገራዊ የሸማቾች መብት ጥበቃ ማህበር የቦርድ አመራሮች የተመረጡ ሲሆን የቦርድ አመራሮቹ በቀጣይ በሚሠራቸው ስራዎች ላይ ስልጠና እና ውይይት ተካሂዳል፡፡

Share this Post