የንግድ ትስስርና ወጪ ንግድ ፕሮሞሽን ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ካሳሁን ጎፌ ከኢራኑ አባሳደር አቶ ሳመድ አሊ ላኪዛድ ጋር ተወያዩ።

የንግድ ትስስርና ወጪ ንግድ ፕሮሞሽን ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ካሳሁን ጎፌ ከኢራኑ አባሳደር አቶ ሳመድ አሊ ላኪዛድ ጋር ተወያዩ። ======================== አዲስ አበባ 04/07/2016ዓ.ም (የንቀትሚ) የንግድ ትስስርና ወጪ ንግድ ፕሮሞሽን ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ካሳሁን ጎፌ በኢትዮጵያ የኢራን አምባሳደር እና በአፍሪካ ህብረት ቋሚ ተወካይ አቶ ሳመድ አሊ ላኪዛድ ጋር በሁለትዮሽ የንግድ ትስስር ዙሪያ ውይይት አድርገዋል:: ኢራን ኢትዮጵያን ጨምሮ በቅርቡ ብሪክስን ከተቀላቀሉ ሀገራት መካከል አንዷ ስትሆን ለሀገራችን ወጪ ምርቶች በተለይም የቡና የጥራጥሬ እና ሌሎች የግብርና ምርቶች ከፍተኛ መዳረሻ ሀገር መሆን የምትችል ሀገር ስለመሆኗ በውይይታቸው አንስተዋል። በቀጣይ የሁለቱ ሀገራትን ንግድ ለማሳለጥ በቅንጅት እና በትኩረት እንደሚሰራ በውይይታቸው ስምምነት ላይ ደርሰዋል::

Share this Post