ለኮሜሳ አባል ሀገራት የተስማሚነት ምዘና አገልገሎት ሰጪ ተቋማት ስልጠና ተሰጠ::

ለኮሜሳ አባል ሀገራት የተስማሚነት ምዘና አገልገሎት ሰጪ ተቋማት ስልጠና ተሰጠ:: =================== አዲስ አበባ 09/07/2016ዓ.ም (ንቀትሚ) በምስራቅና ደቡባዊ አፍሪካ የጋራ ገበያ/COMESA/ አባል ሀገራት ለሚገኙ የተስማሚነት ምዘና አገልግሎት ሰጪ ተቋማት በምርት ሰርተፍኬሽን፣ በአሰራር ስርዓት ሰርተፍኬሽን እና በኢንስፔክስን ዙሪያ በአዲስ አበባ ስልጠና እየተሰጠ ነው፡፡ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር የንግድ ትስስርና ወጪ ንግድ ፕሮሞሽን ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ካሳሁን ጎፌ በስልጠናው ላይ እንደገለጹት የኢትዮጵያ መንግስት ዓለም አቀፍ የጥራት ማረጋገጫ ስርዓቶችን ለማዘጋጀትና ለመተግበር ቁርጠኛ ነው ያሉ ሲሆን ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ የጥራት ደረጃዎች እና በጥራት ቁጥጥር ሂደቶች ላይ ስልጠናዎችን በመስጠት ፈጠራና መሻሻል የታከለባቸው የአመራረት ዘዴዎችን እንደምትደግፍም አስረድተዋል፡፡ የምስራቅና ደቡባዊ አፍሪካ የጋራ ገበያ/COMESA/ ስምምነት አባል ሀገራቱ ለሚያመርቷቸው እና ለሚነግዷቸው ምርቶች የጋራ የጥራት ማረጋገጫ እና የቤተ ሙከራ አሰራር ስርዓቶችን ተግባራዊ በማድረግ በዓለም አቀፍ ደረጃ እውቅና ያለው አገልግሎት መስጠት እንዳለባቸው እንዲሁም የጋራ የጥራት ምልክትና ህግና ስርዓት እንዲኖራቸው ያትታል፡፡ ይህም ሀጋረዊ ፖሊሲዎችንና ሥርዓቶችን ከቀጣናዊ እና ዓለም አቀፋዊው ጋር በማጣጣም የ COMESA አባል ሀገራት ንግድን ለማሳለጥ ያስችላል፣ ከአስፈላጊ ተቋማትና ባለድርሻዎች ጋርም ቅንጅትና ትብብርን ያጠናክራል ሲሉ ሚኒስትር ዴኤታው አብራርተዋል፡፡ በ COMESA ሴክሬታሪያት፣ በጀርመን የስነ- ልክ ኢኒስቲትዩት(PTB) እና በኢትዮጵያ ተስማሚነት ምዘና ድርጅት ትብብር የተዘጋጀውና በምርት ጥራት እና በሰራር ስርዓት ሰርተፍኬሽን እና በኢንስፔክሽን ላያ ያተኮረው ስልጠና ለአምስት ቀናት ይሰጣል።

Share this Post