አስመጪዎች ምርቶችን ወደ ሀገር ውስጥ ከማስገባታቸው በፊት ምን ቅድመ ሁኔታዎችን ሊገነዘቡ ይገባል?

አስመጪዎች ምርቶችን ወደ ሀገር ውስጥ ከማስገባታቸው በፊት ምን ቅድመ ሁኔታዎችን ሊገነዘቡ ይገባል? ================= አዲስ አበባ 29/07/2016ዓ.ም (የንቀትሚ) የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ወደ ሀገር ውስጥ የሚገቡ ምርቶችን ጥራት ያረጋግጣል፣ ከጥራት ደረጃ በታች ሆነው ለተገኙት ምርቶች የእርምት እርምጃ ይወስዳል፡፡ ይህም የጥራት ቁጥጥር ስራ በሁለት መንገድ ይካሄዳል፡፡ 👉የመጀመሪያው አማራጭ ወደ ሀገር ውስጥ የሚገቡ የጥራት ደረጃ የወጣላቸው ምርቶች ወደ ሀገራችን መግቢያ ድንበር ላይ ሲደርሱ ናሙና ተወስዶ በኢትዮጵያ ተስማሚነት ምዘና ድርጅት ላብራቶሪዎች በማስፈተሽ በላብራቶሪው ውጤት መሰረት የጥራት ደረጃውን አሟልተው ሲገኙ እንዲገቡ ካላሟሉ ደግሞ እንዳይገቡ ይደረጋሉ። 👉 ሁለተኛው መንገድ አስመጪዎች ምርቶቹ ከሚመጡበት ሀገር ከተመረጡ ዓለም ዓቀፍ የተስማሚነት ምዘና ተቋማት የጥራት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ይዘው ከቀረቡ ይህንን የምስክር ወረቅት ማሰረጃና የምርቱን ትክክለኛነት በማረጋገጥ ወደ ሀገር እንዲገቡ ፈቃድ ይሰጣል፡፡ ይህ የጥራት ቁጥጥር የሚካሄደው ጥራት በጎደለው ምርት ምክንያት በዜጎች ላይ የሚደርሰውን የጤና፣ የደህንነትና የኢኮኖሚ እንዲሁም በሀገር ላይ የሚያስከትለውን የኢኮኖሚ ጉዳት ለማስቀረት ነው፡፡ ለዚህ ዓላማ ስኬታማነት፣ የቁጥጥር ሂደቱንም ለማቃለል እና የእነሱንም አላስፈላጊ ወጪ ለማስቀረት አስመጪዎች አስቀድመው ማድረግ የሚጠበቅባቸው ነገሮች አሉ፡፡ 👉ማንኛውም አስመጪ ከማስመጣቱ በፊት የሀገራችንን የምርት ጥራት ደረጃዎች ማወቅና የሚያስመጣቸው ምርቶች የሀገሪቱን መስፈርት ማሟላታቸውን ማረጋገጥ አለበት፡፡ 👉ስለሚያስመጣው ምርት ባህሪ በቂ ግንዛቤ ሊኖረው እና የጥራት መስፈርቶችን ከኢትዮጰያ ደረጃዎች ኢንስቲትዩት፣ ከኢትዮጵያ ተስማሚነት ድርጅት እና ከሌሎችም መሰል የሀራችን ተቋማት መውሰድና መረዳት ይጠበቅበታል፡፡

Share this Post