በሰበታ ሀዋስ ወረዳ ተፍኪ ከተማ ላይ የተገነቡ የ10 አቅመ ደካማ ቤቶች ግንባታ ተጠናቀቀ።

በሰበታ ሀዋስ ወረዳ ተፍኪ ከተማ ላይ የተገነቡ የ10 አቅመ ደካማ ቤቶች ግንባታ ተጠናቀቀ። =================== አዲስ አበባ 18/07/2016ዓ.ም (የንቀትሚ) የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ከመደበኛ ስራው ጎን ለጎን ማህበራዊ ሃላፊነቱን ለመወጣት የተለያዩ ተግባራትን እያከናወነ ይገኛል፡፡ በዘንድሮው በጀት ዓመት በኦሮሚያ ክልል ሰበታ ሀዋስ ወረዳ ተፍኪ ከተማ ላይ ፍቃደኛ ባለሀብቶችን በማስተባበር በ10 ሚሊዮን ብር ደረጃቸውን የጠበቁ የ10 አቅመ ደካማ መኖሪያ ቤቶችን አስገንብቶ ማጠናቀቁን የሚኒስቴር መስራ ቤቱ የሚኒስትር ጽ/ቤት ሃላፊ ወ/ሮ ፍሬህይወት ወልደማሪያም አስታወቁ፡፡ አመራሩ በሰጠው ልዩ ትኩረት የቤቶቹ ግንባታ በአጭር ጊዜ ውስጥ መጠናቀቅ እንዲችል አስተዋጽኦ አድርጎል ያሉት ሀላፊዋ የተገነቡት ቤቶች ባለ 3 ክፍል ሲሆኑ ጾታንና አካል ጉዳተኞችን ያማከሉ መሆናውን ተናግረዋል፡፡ የተገነቡት ቤቶችም በቅርቡ እርክክብ ለማድረግ ስራዎች እየተሰሩ መሆናቸውን ሀላፊዋ ጠቁመዋል፡፡ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከ2015ዓ.ም ጀምሮ አስካሁን ድረስ 77 የአቅመ ደካማ ቤቶች ገንብቷል፡፡

Share this Post