ጉድለት በተገኘባቸው 12 ነዳጅ አምጪ ቦቴዎች ላይ አስተዳዳራዊ እርምጃ ተወሰደ

ጉድለት በተገኘባቸው 12 ነዳጅ አምጪ ቦቴዎች ላይ አስተዳዳራዊ እርምጃ ተወሰደ =========================== አዲስ አበባ 6/07/2016ዓ.ም (ንቀትሚ) የህብረተሰቡ ጤናና፣ደህንነት ለማስጠበቅ ብሎም ሸማቹ ማህበረሰብ ላወጣው ወጪ ተመጣጣኝ ክብደት ያገኘ መሆኑን ለማረጋገጥ የተለያዩ የታሸጉ ምርቶችን እንዲሁም የፈሳሽ የተጣራ ክብደትና የመለኪያ መሳሪያዎችን ትክክለኛነት የማረጋገጥ ስራ በትኩረት እየተሰራ ይገኛል፡፡ በንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር የሕጋዊ ስነ ልክና ቴክኒክ ደንብ ማስተባበሪያ መሪ ስራ አስፈፃሚ አቶ ጌታቸው ወለል የህብረተሰቡን ጤንነት ከመጠበቅ አኳያ ለልኬት የሚያገለግሉ የህክምና መሳሪያዎች ትክክለኛነት የማረጋገጥ ስራ እንደሚሰራ ጠቅሰው በጤና ተቋማት የሚገኙ መሳሪያዎች በሙሉ በአስገዳጅ ደረጃ የሚያልፉ መሆናቸውን ገልፀዋል፡፡ ባለፉት ስድስት ወራት 18 ምርቶች ላይ የተጣራ ክብደት ለማረጋገጥ እቅድ ተይዞ በ16 ምርቶች ላይ ፍተሻ በማድረግ ትክክለኛነታቸውን የማረጋገጥ ስራ መከናወኑን የተናገሩት መሪ ስራ አስፈፃሚው ጥቆማ በቀረበባቸውና ጉድለት በተገኘባቸው 12 ነዳጅ አምጪ ቦቴዎች ላይ አስተዳዳራዊ እርምጃ መወሰዱን መሪ ስራ አስፈጻሚው አስታውቀዋል፡፡ ህብረተሰቡ ለከፈለው ዋጋ ተመጣጣኝ ያልሆነ የዕቃ ክብደት ሲያጋጥመው በየደረጃው ላሉ የንግድ ዘርፍ መዋቅሮች ጥቆማ እንዲሰጥ ሲሉ አቶ ጌታቸው መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

Share this Post