የኢትዮጵያ ምርት ገበያ አካዳሚ የ 3ኛ ዙር ሰልጣኖቹን አስመረቀ

የኢትዮጵያ ምርት ገበያ አካዳሚ የ 3ኛ ዙር ሰልጣኖቹን አስመረቀ =================== አዲስ አበባ 14/06/2016ዓ.ም (የንቀትሚ) የኢትዮጵያ ምርት ገበያ አካዳሚ በቡና ቅምሻ እና ደረጃ በ 3ኛ ዙር ያሰለጠናቸውን 20 ሰልጣኞች ዛሬ አስመርቋል፡፡ ምርት ገበያው ምርቶችን ከማገበያየትና ደረጃ ከማውጣት በተጨማሪ በከፈተው አካዳሚ የሀገራችን ቡና በጥራትና በደረጃ እሴት ተጨምሮበት እንዲገበያይና ለሀገር የሚገባውን ኢኮኖሚ እንዲያስገኝ አስፈላጊ የሆነ በሙያው የሰለጠነ የሰው ሀይል ለማፍራት እየሰራ እንደሚገኝ የኢትዮጵያ ምርት ገበያ ምክትል ስራ አስኪያጅ አቶ በሀይሉ ንጉሴ ተናግረዋል፡፡ ተቋሙ ለአመታት ግብይት በማካሄድና ደረጃ በማውጣት ያገኘውን ልምድ መሰረት በማድረግ በከፈተው አካዳሚ ከ 1ኛ እስከ 3ኛ ዙር 52 ሰልጣኖችን ያስመረቀ ሲሆን በዛሬው እለት ለሦስት ወራት በተግባርና በንድፈ ሀሳብ የተደገፈ ስልጠናቸውን በብቃት ያጠናቀቁ ሰልጣኞችን ሲያስመርቅ በቆይታቸው ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ አራት ሰልጣኞች ልዩ የምስክር ወረቅትና የዋንጫ ሽልማት አበርክቷል፡፡ ለዘመናዊ የግብይት ስርዓት መሰረት የጣለው የኢትዮጵያ ምርት ገበያ ህግ፣ እውቀት እና ቴክኖሎጂን በመጠቀም የኢትዮጵያን የወጪ ንግድ ምርቶች አይነትና ጥራት በማሻሻል የውጪ ምንዛሪ ግኝትን ለማሳደግ አበክሮ እየሰራ እንደሚገኝ ምክትል ኃላፊው አብራርተዋል፡፡

Share this Post