ከ930 በላይ የቅዳሜና እሁድ ገበያ ማዕከላት ተዘርግተዋል።

ከ930 በላይ የቅዳሜና እሁድ ገበያ ማዕከላት ተዘርግተዋል። ======================= አዲስ አበባ 05/06/ 2016ዓ.ም (ንቀትሚ) የዋጋ ንረትን ለማረጋጋት በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍል ከ 930 በላይ የቅዳሜና እሁድ ገበያዎች የተዘረጉ ሲሆን እነዚህ ገብያዎች ለህገ-ወጦች እና ደላላዎች አንዳይጋለጡ ክትትና ቁጥጥር ማድረግ እንደሚገባ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር አቶ ገብረመስቀል ጫላ ተናገሩ፡፡ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ የመጣውን የዋጋ ንረት ለማርገብ መንግስት ከወሰዳቸው እርምጃዎች ውስጥ የቅዳሜና እሁድ ገበያን ማስፋፋት አንዱ ሲሆን በአሁኑ ሰዓት በመላ ሀገሪቱ ከ930 በላይ የቅዳሜና እሁድ ገበያ ማእከላት ይገኛሉ፡፡ በእነዚህ የግብይት ማእከላት የግብርና እና የኢንዱትሪ ምርቶች በአጠረ የግብይት ሰንሰለት ከመደበኛው ገበያ ከ10-50 ብር በሚደርስ ቅናሽ እየቀረቡ መሆኑን የጠቀሱት ሚኒስትሩ የግብይት ቦታዎችን ቁጥር ከማስፋት ጎን ለጎን በቂ ምርት እንዲቀርብባቸው ማድረግ፣ ግብይቱን ማዘመን እና ለህገ-ወጦች እና ደላላዎች እንዳይጋለጡ ጥብቅ ድጋፍና ክትትል ማድረግ በየደረጃው ከሚገኝ አመራር የሚጠበቅ ቁልፍ ተግባር ነው ብለዋል፡፡ ሚኒስትሩ እንደገለጹት ባለፉት 6 ወራት የዋጋ ንረትን ለመቆጣጠር የተለያዩ የፖሊሲ እርጃዎች ተወስደዋል፡፡ በሀገር ውስጥ የሚመረቱ የግብርና እና የኢንዱትሪ ምርቶችን፣ በፍራንኮ ቫሉታና በሌሎች አማራጮች የሚገቡ የፍጆታ ምርቶቸን አቅርቦት ለማሳደግ በተሰሩ ስራዎች እንዲሁም በንግድ ሴክተሩ በተከናወኑ የገበያና ዋጋ ማረጋጋት ስራዎች ባለፈው በጀት ዓመት 34.2 በመቶ የነበረው አጠቃላይ የዋጋ ግሽበት ባለፉት 6 ወራተ አንፃራዊ መረጋጋገት በማሳየት በህዳር ወር ወደ 28.3 በመቶ ዝቅ ብሏል፡፡ ይህንን ውጤት አጠናክሮ ወደሚፈለገው ደረጃ በማድረስ የህብረተሰቡን ኑሮ ጫና ማቃለል የቀጣይ ቁልፍ ተግባር መሆኑንም አመላክተዋል፡፡

Share this Post