2016 በጀት ዓመት ስምንት ወራት ቦሎቄ ምርት 4,581.2 ቶን ለማዕከላዊ ገበያ መቅረቡን የሲዳማ ክልል ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ አስታወቀ፡፡

2016 በጀት ዓመት ስምንት ወራት ቦሎቄ ምርት 4,581.2 ቶን ለማዕከላዊ ገበያ መቅረቡን የሲዳማ ክልል ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ አስታወቀ፡፡ ==================== አዲስ አበባ 12/07/2016 ዓ.ም(ንቀትሚ) የሲዳማ ንግድና ገበያ ቢሮ ኤክስፖረት ምርቶች ላይ ሕጋዊ ግብይት ሥርዓት ለማስፈን ትኩረት ተሰጥተው እየሰራ ይገኛል፡፡ በዓለም ገበያ ሊያወዳደሩን ይችላሉ ተብሎ ከተለዩት ግብርና ምርቶች ውስጥ ከቡና እና ሰሊጥ ቀጥሎ የጥራጥሬ ምርት መሆኑን የሚታወቅ ሲሆን እነዚህ ጥራጥሬ ኤክስፖርት ምርቶች በሲዳማ ክልል በ11 ወረዳዎች በስፋት ይመረታል፡፡ በ2016 በጀት ዓመት ስምንት ወራት ቦሎቄ አምራች ወረዳዎች አማካይነት ቀይ ቦሎቄ 3,933.2 ቶን እና ቡራቡሬ ቦሎቄ 648 ቶን አጠቃላይ 4,581.2 ቶን ወደ ማዕከላዊ ገበያ መቅረቡን የግብይት ማስፋፈያ ዳይሬክቶሬት ተወካይ አቶ መልካሙ መና ገልፀዋል፡፡ የመጀመሪያ ደረጃ ግብይት ማዕከላት ተደራሽ ያለመሆን፣ ኮንትራት የገቡ ባለሃብቶች በሙሉ አቅማቸው ወደ ግብይት ያለመግባት፣የኢትጵያ ምርት ገበያ የቦሎቄ ዋጋ ከአከባቢው ገበያ ዋጋ ያነሰ መሆን፣ባለድረሻ አካላት ተቀናጅተው ያለመስራትና ኮንትሮባንድ ንግድ የዘርፉ ተግዳደሮቶች መሆኑ አቶ መልካሙ ተናግረዋል።

Share this Post