በንግዱ ዘርፍ የተገኘው አፈፃፀም በሀገራዊ የኢኮኖሚ እድገት ላይ ያለው አስተዋፅኦ ከፍተኛ ነው:-የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ፍሠሃ ይታገሱ(ዶ/ር)

በንግዱ ዘርፍ የተገኘው አፈፃፀም በሀገራዊ የኢኮኖሚ እድገት ላይ ያለው አስተዋፅኦ ከፍተኛ ነው:-የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ፍሠሃ ይታገሱ(ዶ/ር) =================== አዲስ አበባ 13/10/2016ዓ.ም (ንቀትሚ) የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር በ2016 በጀት አመት የ10 ወራት እቅድ አፈፃፀም እና በዋና ዋና የማክሮ ኢኮኖሚ አፈጻጸም ላይ ከአጠቃላይ ሰራተኞች ጋር ውይይት አካሂዷል። እየተገባደደ ባለው በ2016 በጀት አመት ከእቅድ አንፃር የተሻለ አፈፃፀም መገኘቱን የገለፁት የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ፍሠሃ ይታገሱ (ዶ/ር) በንግዱ ዘርፍ የተገኘው አፈፃፀም በሀገራዊ የኢኮኖሚ እድገት ላይ ያለው አስተዋፅኦ ከፍተኛ እንደሆነም ገልፀዋል። ሀገራዊ የማክሮ ኢኮኖሚ አፈፃፀም እና የበጀት አመቱ የ10 ወራት እቅድ አፈፃፀም ለአጠቃላይ የተቋሙ ሰራተኞች መቅረቡ ሀገራዊ ግቦችን ለማሳካት ጠቃሚ እንደሆነም ተገልፃል። በበጀት አመቱ በቀሩ ጊዜያት የተገኙ ውጤቶችን በማስቀጠል ዝቅተኛ አፈፃፀም የተገኘባቸው ዘርፎችን በመለየት በርብርብ መስራት እንደሚገባ ሚኒስትር ዴኤታው አሳስበዋል።

Share this Post