የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ከ ጂ አይ ዜድ ጋር በንግድ ስራ አመቺት ዙሪያ በጋራ ለመስራት የሚያስችለውን የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረመ

የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ከ ጂ አይ ዜድ ጋር በንግድ ስራ አመቺት ዙሪያ በጋራ ለመስራት የሚያስችለውን የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረመ ====================== አዲስ አበባ 26/10/2015ዓ.ም (ንቀትሚ) የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር የጥራት መሠረተ ልማት ማረጋገጫ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ እንዳለው መኮንን ከጂ አይ ዜድ ጋር የንግድ ስራን አመቺ ለማድረግ እና በዘርፉ በጋራ ለመስራት የሚያስችል የመግባቢያ ሠነድ ተፈራርመዋል፡፡ የንግድ ስራ ምቹና ውጤታማ እንዲሆን የንግድ ዘርፉን በቴክኖሎጂ መደገፍ ይገባል ያሉት ሚኒስትር ዴኤታው የተለያዩ ሪፎርሞችን በማካሄድ መመሪያዎችን የማሻሻልና አላስፈላጊ መስፈርቶችን የማስቀረት ስራዎች መሰራታቸውንም ጠቅሰዋል፡፡ የመግባቢያ ሠነዱ መፈረም ቀደም ብለው እየተሠሩ የነበሩ የንግድ ስራ አመቺነት ስራዎችን ለማጠናከር እና ምቹ፣ ቀልጣፋና ዲጂታል የንግድ አገልግሎትን ለማጠናከር እንደሚያግዝ ተናግረዋል፡፡

Share this Post