የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት መገለጫዎች

የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት መገለጫዎች =================== አዲስ አበባ 14/02/2016ዓ.ም (ንቀትሚ) የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ሀገርን ሲጠብቅ፣ የሕዝብን ሰላም ሲያስከብርንና በተሰማራባቸው ሁሉ ተልዕኮውን ሲፈፅም ምንጊዜም የማይሽራቸው፣ የሚታወቅባቸው መገለጫዎችና እሴቶች አሉት፡፡ እነዚህ እሴቶች የመከላከያ ሠራዊት አባላት በግዳጅ አፈፃፀምም ኾነ በማንኛውም ወቅት የሚተገብሯቸው ናቸው፡፡ የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ቁልፍ እሴቶች የሚከተሉት ናቸው፡፡ 1. ከራስ በፊት ለሕዝብና ለሀገር ጥቅም መከላከያ ሠራዊታችን ምንግዜም ለሕዝብና ለሀገር ጥቅም ቅድሚያ ይሰጣል፡፡ የሕዝብና የሀገርን ጥቅም የሚፃረሩ ተግባራትን በሙሉ ለማክሸፍ ሌት ተቀን ይተጋል፡፡ ለሀገር መከላከያ ሠራዊት አባላት ማንኛውም ነገር ከሕዝብና ከሀገር ጥቅም በታች ነው፡፡ 2. ምንጊዜም የተሟላ ስብዕና የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት አባላት በየዕለቱ በዕውቀትና በአካል ራሳቸውን አዘጋጅተው በተሟላ ሰብዕና ሀገራቸውን ያገለግላሉ፡፡ ወታደራዊ ሥነ-ሥርዓት የሚጠይቀውን ባህሪ በመላበስ ግዳጃቸውን ይወጣሉ፡፡ 3, ያልተሸራረፈ ሰብአዊነትና ዴሞክራሲያዊ አስተሳሰብ የመከላከያ ሠራዊት አባላት እኩልነት፣ ሕብረብሔራዊ አንድነት፣ ሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ አስተሳሰብ መገለጫ ባህሪያቸው ነው፡፡ በማንአለብኝነት ሳይኾን በመከባበርና በመተማመን እሳቤ የሚመሩት የመከላከያ ሠራዊት አባላት፤ የሕዝብን ሰብኣዊና ዴሞክራሲያዊ መብት አክብረው ያስከብራሉ፡፡ 4, በማንኛውም ግዳጅ ወይም ተግባር የላቀ ውጤት ድል የመከላከያ ሠራዊት አባላት የዘወትር መገለጫ ነው፡፡ በማንኛውም ተልዕኮ የላቀ ውጤት ማስመዝገብ የመከላከያ ሠራዊታችን ባህሪ ነው፡፡ የኢትዮጵያ ወታደሮች በልማት፣ በሰላም ማስከበርና በጦር ግንባር የላቀ ውጤት ማስመዝገብ የማንነታቸው አንዱ አካል ነው፡፡

Share this Post