በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ የጠረፍ ንግድ ፈቃድ በኦንላይን መሰጠት ተጀመረ።

======================= አዲስ አበባ 21/10/2016ዓ.ም (የንቀትሚ) በአፋር ክልል ከጁቡቲ ድንበር በ50 ኪሎ ሜትር ራዲየስ ውስጥ የሚገኙ የድንበር አካባቢ ነዋሪዎችን በጠረፍ ንግድ ተጠቃሚ ለማድረግ ከ ሰኔ 21 ቀን 2016 ዓ.ም የጠረፍ ንግድ ፈቃድ በኦንላይን ለመጀመሪያ ጊዜ መስጠት ተጀምሯል፡፡ በጠረፍ ንግድ ፈቃድ አሰጣጥ እና የጉምሩክ የአሰራር ስርዓት ዙሪያ ለጠረፍ ነገዴዎች እና ባለድርሻ አካላት ከሰኔ 20-21 ቀን 2016 ዓ.ም በአፋር ክልል ሰመራ ከተማ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና እየተሰጠ የሚገኝ ሲሆን ከስልጠናው ጎን ለጎን በንግድ ምዝገባ፣ ፈቃድ እና ድህረ ፈቃድ ኢንስፔክሽን መመሪያ ቁጥር 935/2015 መሰረት መስፈርቱን ለሚያሟሉ የጠረፍ ነጋዴዎች የጠረፍ ንግድ ፈቃድ በኦንላይን እየተሰጠ ይገኛል፡፡ የጠረፍ ንግድ ፈቃድ በኦንላይን የተሰጣቸው በአፋር ክልል ከጂቡቲ ድንበር በ50 ኪሎ ሜትር ራዲየስ ውስጥ ከሚገኙ የድንበር አካባቢዎች ማለትም ከኤልዳአር፣ አፋምቦ፣ አሳይታ እና ገረኔ ወራዳዎች የጠረፍ ንግድ እንዲነግዱ በአካባቢው ማህበረሰብ ተሳትፎ የተመረጡ ነጋዴዎች ናቸው፡፡ በሶማሌ ክልል ከአይሻ፣ ገብለሎ እና አዲጋላ ወረዳዎች የጠረፍ ንግድ እንዲንግዱ በማህበረሰቡ ተሳትፎ ለተለዩት ነጋዴዎችም ከሚቀጥለው ሳምንት ጀምሮ የጠረፍ ንግድ ፈቃድ በኦንላይን የሚሰጥ ይሆናል

Share this Post