የምግብ ደህንነት በዘላቂነት ለማረጋገጥ የጥራት ስርዓት መዘርጋትና ግንዛቤ መፍጠር ትኩረት ተሰጥቶት ሊሰራ እንደሚገባ ተገለፀ፡፡

የምግብ ደህንነት በዘላቂነት ለማረጋገጥ የጥራት ስርዓት መዘርጋትና ግንዛቤ መፍጠር ትኩረት ተሰጥቶት ሊሰራ እንደሚገባ ተገለፀ፡፡ ========================= አዲስ አበባ 30/09/2016ዓ.ም(ንቀትሚ) አለም አቀፍ የምግብ ደህንነት ቀን ዛሬ በዓለም ለ6ኛ ጊዜ በአገራችን ደግሞ ለ5ኛ ጊዜ ‹‹ በምግብ ደህንነት ዙሪያ ለሚከሰቱ ያልታሰቡ ችግሮች እንዘጋጅ›› በሚል መሪ ቃል እየተከበረ ይገኛል፡፡ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚንስቴር የጥራት መሰረተ ልማትና ማረጋገጫ ዘርፍ ሚንስትር ዲኤታ አቶ እንዳለው መኮንን በበዓሉ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት የአለም የምግብ ደህንነት ቀንን ለማክበር በአንድነት ስንሰባሰብ የምግብ ደህንነት ከፍተኛ ደረጃዎችን ለማክበር፣ በምግብ ምርትና ስርጭት ላይ ግልፅነትን ለማስፈን እና ግለሰቦች ስለ ምግብ በመረጃ የተደገፈ ምርጫ እንዲያደርጉ በእውቀትና ሃብት ለማበረታታት ያለንን ቁርጠኝነት ልናረጋግጥ ይገባል ብለዋል። በዚህ ዘመን የምግብ ደህንነትን የማረጋገጥ ተግዳሮቶች እና እድሎች ከመቼውም ጊዜ በበለጠ ጉልህ በሆኑበት ወሳኝ ወቅት ላይ ቆመናል ያሉት ሚንስትር ዲኤታው የምግብ ደህንነት የግል ደህንነት ጉዳይ ብቻ ሳይሆን እያንዳንዱን ግለሰብ የሚነካ መሰረታዊ ሰብአዊ መብት ነው በማለት ጤናማ ያልሆኑ የምግብ አሰራሮች ከምግብ ወለድ በሽታዎች እስከ ኢኮኖሚያዊ ችግሮች እንዲሁም ወደ ማህበራዊ አለመረጋጋቶች ያመራሉ ሲሉ ተናግረዋል። በዓሉን ምክንያት በማድረግ የተለያዩ የፓናል ውይይቶች የተካሄዱ ሲሆን ከኢትዮጵያ የደረጃዎች ኢንስቲትዩት ከግብርና ሚንስቴር እና ከኢትዮጵያ ምግብና መድሀኒት ቁጥጥር ባለስልጣን ጋር በመተባበር ለሚድያ አመራሮችና ባለሙያዎች እና ሌሎች ባድርሻ አካት ጋር በጋራ በመሆን የምክክርና ግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ በማካሄድ ተከብሯል ።

Share this Post