የኢትዮጵያ እና የብራዚልን የንግድ ሚዛን ለማሻሻል ሁለቱ ሀገራት በጋራ ይሰራሉ

የኢትዮጵያ እና የብራዚልን የንግድ ሚዛን ለማሻሻል ሁለቱ ሀገራት በጋራ ይሰራሉ ====================== አዲስ አበባ 28/10/2016ዓ.ም (የንቀትሚ) ኢትዮጵያ ወደ ብራዚል የምትልካቸውን ምርቶች መጠን በማሳደግ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን የንግድ ሚዛን ለማሻሻል በቅንጅት እንደሚሰሩ የንግድና ቀጣናዊ ትስስትር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ(ዶ/ር) ገለጹ፡፡ ሚኒስትሩ በዛሬው እለት ከብራዚል ልኡካን ጋር የሁለቱን ሀገራት ግንኙነትና የንግድ ልውውጥ ማጠናከር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል፡፡ ኢትዮጵያ እና ብራዚል የብሪከስ(BRICS) አባል እንደመሆናቸው መጠን የንግድ ግንኙነታቸውንና ወዳጅነታቸውን ማጠናከር ያስፈልጋል ያሉት ሚኒስትሩ ወደ ብራዚል ኤክስፖርት የሚደረጉ ምርቶችን በማሳደግ እንዲሁም ኢትዮጵያ በንግድና ኢንቨስትመንት ባላት እምቅ ሀብት ብራዚላዊያን መጥተው ኢንቨስት በማድረግ የሁለትዮሽ የንግድ ግንኙነትን ይበልጥ ማጎልበት የስፈልገናል ሲሉም አስረድተዋል፡፡ በቁም እንሰሳት ንግድ ዘርፍ ከብራዚል ልምድ ለመውሰድ፣ ሁለቱም በግብርናው ዘርፍ እና በማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ በጋራ ለመስራት እና የንግድ ግንኙነታቸውን ለማጎልበት በቀጣይነት ለመምከርና ስምምነቶችን ለመፈራረም በውይይታቸው ከስምምነት ተደርሷል፡፡

Share this Post