Sultan Instant Full Cream Milk Powder (400g), (PD 19/02/2024, & Exp 18/02/2026 B.NO

Sultan Instant Full Cream Milk Powder (400g), (PD 19/02/2024, & Exp 18/02/2026 B.NO.56 እና Nura Super Instant Full Cream Milk Powder (400g) PD 01/11/2023 እና Exp 31/10/2025 BT 23246006 LOT No. 230915 291123003127 የሆኑ የወተት ምርቶች የደህንነትና የጥራት መስፈርቶችን ያላሟሉ በመሆኑ ህብረተሰቡ እንዳይጠቀማቸው ======================= አዲስ አበባ 27/09/2016ዓ.ም (ንቀትሚ) የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር በገበያ ላይ በመገኘት የገበያ ኢንስፔክሽን ስራ በማከናወን ከገበያ ከተወሰደው SULTAN INSTANT FULL CREAM MILK POWDER (400g), (PD 19/02/2024, & Exp 18/02/2026 B.NO.56 እና Nura Super Instant Full Cream Milk Powder (400g) PD 01/11/2023 እና Exp 31/10/2025 BT 23246006 LOT No. 230915 291123003127 ወካይ ናሙና ላይ በተደረገው የላበራቶሪ ፍተሻ ውጤት መሰረት protein %by mass, Arsenic (as As) mg/kg, & zinc (as Zn) mg/kg CES 280፡2021 የተደነገገውን የጥራት መስፈርት ሳያሟሉ የተገኙ ምርቶች በመሆናቸው ህብረተሰቡ ከላይ በ400ግራም የተጠቀሱ ባች ቁጥር ምርቶችን እንዳይጠቀመው ሲል ሚኒስቴር መስራቤቱ አስታውቋል:: የህብረተሰቡን ጤናና ድህነት እንዲሁም ጥቅም ከመጠበቅ አንጻር ሸማቹ ህብረተስብ ይህን ከላይ የተጠቀሰውን ባች ምርት እንዳይጠቀም በየደረጃው ባለው የክልል እና የከተማ አስተዳደር ንግድ እንዲሁም የጤና ቢሮዎች በኩል ለህብረተሰቡ ግንዛቤ እንዲሰጥ እና ጥብቅ ክትትልና ቁጥጥር እንዲደረግ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ እያሳሰበ በገበያ ቦታ እና ሱፐር ማርኬት ማንኛውም ነጋዴ ሆነ ግለሰብ ሲሸጥ ከተገኙ አስፈላጊው አስተዳደራዊ እና ህጋዊ እረምጃዎች እንደሚወሰድ ሚኒስቴር መስራቤቱ አስታውቋል፡፡

Share this Post