የኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት
ኢተምድ የሚለው ምህፃረ ቃል ፡ የኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት” ይወክላል፡፡ ኢተምድ በጥር ወር 2003ዓ.ም በሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 196/2003 በፌደራል ደረጃ የመንግስት የልማት ድርጅት ሆኖ የተስማሚነት ምዘና አገልግሎቶችን ለመስጠት ተቋቁሟል፡፡ የድርጅቱ ተቆጣጣሪ ባለስልጣን የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ነው፡፡ ኢተምድ በዋነኝነት የተስማሚነት ምዘና አገልግሎቶች ማለትም የላብራቶር ፍተሻ፣ የኢንስፔክሽንና የሰርቲፊኬሽን አገልግሎት የሚሰጥ ሲሆን በስሩ ከ200 በላይ ሰራተኞችን ይዞ 8ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች በመላው ሀገሪቱ በማደራጀት እየሰራ የሚገኝ ድርጅት ነው፡፡
አድራሻገርጂ